Weblinks
Resources » News Content » News
Results 1 - 2 of 2
|
News Content/News
Author:Administrator
ዚያራሐረሪዎች ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ እንዲሁም ባህላዊ ተግባራቸውን ጠብቀው ለረጅም ጊዜ ያቆያቸውና ለወደፊትም ዋስትና ከሚሰጣቸው ተግባራቸው መካከል አንዱ "ዚያራ" ማድረጋቸው ነው፡፡ |
|
News Content/News
Author:Administrator
(በየማነ ናግሽ) Repoterየሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና የሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አንድ ግንባር ቋመፍጠር መስማማታቸውን አሳወቁ፡፡የሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ሐዴድ) ሊቀመንበር አቶ አብዲ ሰብሪ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት፣ ፓርቲያቸው ከሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሐዴፓ) ጋር ለመቀናጀት የወሰነው፣ በቅርቡ አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተስማሙበት የምርጫ ስነምግባር ሰነድ መውጣትን ተከትሎ ነው፡፡ "ሰነዱ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶችን ማቀራረብ ይቻላል የሚል ሃሳብ እንዲኖረን አድርጎናል" ያሉት አቶ ሰብሪ፣ ስምምነቱ በተለይ ተመሳሳይ አቋምና በተመሳሳይ አካባቢ የሚንቀሳቀሱት የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ እንዲሰሩ የሚያነሳሳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ "ሰነዱ አብሮ መሥራት አስተምሮናል፡፡ የመግባባት መንፈስ ፈጥሮብናል"፡፡ በግንባር ለመደራጀት የወሰኑት ሁለቱ ፓርቲዎች በተለይ በመጪው ምርጫ አብሮ መሥራት ውጤት እንደሚኖረውና ለሐረሪ ሕዝብ ትልቅ ጥቅም እንደሚኖረው ይገልፃሉ፡፡ሃዲድ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚያምን ተቃዋሚ ሲሆን፣ ከሐዴፓ ጋር የቀረበ የፖለቲካ ፕሮግራም እንዳለው አቶ አብዲ ይገልፃሉ፡፡ ሐዴድና ሐዴፓ በሐረሪ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች ሲሆኑ፣ የሁለቱም ግንባር ለሐረሪ ሕዝብ ጥቅም እንደሚቆም ገልፀዋል፡፡ |
Powered by Harar Network 4.0.11 © 2005-2010 - All rights reserved
