Harar Network

Tuesday, 17 November 2009 18:27 - ሁለት የሐረሪ ክልል ተቃዋሚ ...
(በየማነ ናግሽ) Repoter

የሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና የሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አንድ ግንባር ቋመፍጠር መስማማታቸውን አሳወቁ፡፡

የሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ሐዴድ) ሊቀመንበር አቶ አብዲ ሰብሪ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት፣ ፓርቲያቸው ከሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሐዴፓ) ጋር ለመቀናጀት የወሰነው፣ በቅርቡ አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተስማሙበት የምርጫ ስነምግባር ሰነድ መውጣትን ተከትሎ ነው፡፡ "ሰነዱ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶችን ማቀራረብ ይቻላል የሚል ሃሳብ እንዲኖረን አድርጎናል" ያሉት አቶ ሰብሪ፣ ስምምነቱ በተለይ ተመሳሳይ አቋምና በተመሳሳይ አካባቢ የሚንቀሳቀሱት የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ እንዲሰሩ የሚያነሳሳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ "ሰነዱ አብሮ መሥራት አስተምሮናል፡፡ የመግባባት መንፈስ ፈጥሮብናል"፡፡ በግንባር ለመደራጀት የወሰኑት ሁለቱ ፓርቲዎች በተለይ በመጪው ምርጫ አብሮ መሥራት ውጤት እንደሚኖረውና ለሐረሪ ሕዝብ ትልቅ ጥቅም እንደሚኖረው ይገልፃሉ፡፡

ሃዲድ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚያምን ተቃዋሚ ሲሆን፣ ከሐዴፓ ጋር የቀረበ የፖለቲካ ፕሮግራም እንዳለው አቶ አብዲ ይገልፃሉ፡፡ ሐዴድና ሐዴፓ በሐረሪ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች ሲሆኑ፣ የሁለቱም ግንባር ለሐረሪ ሕዝብ ጥቅም እንደሚቆም ገልፀዋል፡፡

Tuesday, 17 November 2009 18:26 - ሐረሪዎች ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ...
ዚያራ

ሐረሪዎች ማኅበራዊና  ሃይማኖታዊ እንዲሁም ባህላዊ ተግባራቸውን ጠብቀው ለረጅም ጊዜ ያቆያቸውና ለወደፊትም ዋስትና ከሚሰጣቸው ተግባራቸው መካከል አንዱ "ዚያራ" ማድረጋቸው ነው፡፡
"ዚያራ" ማለት "አዋች" ወይም "ኢናያች" ጉብኝት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የአዋች እና ኢናያች ትርጉም የተጠበቀ ሆኖ ለምድራዊውም ሆነ ለመንፈሳዊ ሕይወት ተገቢነት ያለውን ሰብዕናቸው በአርአያነት ለመጎናፀፍ የሚደረግ ተግባር ነው፡፡

አዋች ሆኑ ኢናያች የተለያዩ ጎብኚዎችን ስለሚያስተናግዱ በቦታው ለጎብኚዎች አስተማሪ፣ መካሪ፣ መንፈሳዊ ሕይወትን አዳሽና ቀስቃሽ እና አስታዋሽ ይሆናሉ፡፡ እነሱም በአገሬው አጠራር ሙሪድ ይባላሉ፡፡

ሙሪድ ባለበት ወይም የሚገኝበት አዋችም ሆኑ ኢናያች ኃላፊነት የሚሰማው ጎብኚዎችን ማስተማር /ማስረዳት/ የሚችል ቦታውን ከጉዳት የሚጠብቅ ሆኖ ባብዛኛው ከቅድመ አያቶች ሲወርድ የተያያዘ የሥጋ ዝምድና ያላቸው ናቸው፡፡

የዚያራ ትግበራ ለጉብኘት ወደ አዋች የሚሄዱ ግለሰብ እንደአቅሙ /ችሎታው/ ስጦታ ያበረክታሉ፡፡ ይህም ገቢ ለአስተዳዳሪዎች እንዲሁም ለምስኪኖች በሙሪዱ አማካይነት ይከፈላል፡፡ ስጦታን የማበርከት ግዴታ በማንም ጎብኚ የለበትም፡፡ መጠኑም በሰጪው ፍላጎት መሠረት ነው፡፡

ሐረሪዎች ንፁህ ናቸው፡፡ ቤታቸውንና አካባቢያቸውን በየዕለቱ የማፅዳት ባሕል አላቸው፡፡ ንፁህ አካባቢ ማራኪ መአዛ ማጠን ልምዳቸው፤ በአዋችም ሆነ በኢናያች ይስተዋላል፡፡ በንፁህና ማራኪ መአዛ በታወደው ቦታ መንፈሳዊ ጥንካሬን በማበረታታት ወደ ፈጣሪያቸው አቤት ይላሉ፡፡ ለዚህም ነው እጣን ከቤታቸው የማያጡት፡፡ በየአዋቹም በዚሁ የሚታወደው ለሙስሊሙ ዱአ ማድረግ ከሃይማኖታዊ ተግባራት መካከል አንዱ ነው፡፡ ዱአ ማለት ከፈጣሪ በጎን ለማግኘት የሚደረግ ፀሎት ማለት ነው፡፡ ዱአ ለማድረግ ደግሞ መልካም ጠረንና ደስታን የሚያውድ፣ መንፈስን ወደ ፈጣሪ ልብን የሚያረጋጋ ሽታ አስፈላጊ በመሆኑ ዕጣን /ሊባነት/ ዑድ ለዚህ ያገለግላሉ፡፡
(መፍቱህ ዘከሪያ እብዱላሂ ኑር፤ የከተማ ባሕል መፍለቂያ፣ 2000