No account yet?
Written by Administrator    Tuesday, 17 November 2009 18:26    PDF Print E-mail
ሐረሪዎች ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ እንዲሁም ባህላዊ ተግባራቸውን ጠብቀው ለረጅም ጊዜ ያቆያቸውና ለወደፊትም ዋስትና ከሚሰጣቸው ተግባራቸው መካከል አንዱ "ዚያራ" ማድረጋቸው ነው፡፡
Hear this article

ዚያራ

ሐረሪዎች ማኅበራዊና  ሃይማኖታዊ እንዲሁም ባህላዊ ተግባራቸውን ጠብቀው ለረጅም ጊዜ ያቆያቸውና ለወደፊትም ዋስትና ከሚሰጣቸው ተግባራቸው መካከል አንዱ "ዚያራ" ማድረጋቸው ነው፡፡
"ዚያራ" ማለት "አዋች" ወይም "ኢናያች" ጉብኝት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የአዋች እና ኢናያች ትርጉም የተጠበቀ ሆኖ ለምድራዊውም ሆነ ለመንፈሳዊ ሕይወት ተገቢነት ያለውን ሰብዕናቸው በአርአያነት ለመጎናፀፍ የሚደረግ ተግባር ነው፡፡

አዋች ሆኑ ኢናያች የተለያዩ ጎብኚዎችን ስለሚያስተናግዱ በቦታው ለጎብኚዎች አስተማሪ፣ መካሪ፣ መንፈሳዊ ሕይወትን አዳሽና ቀስቃሽ እና አስታዋሽ ይሆናሉ፡፡ እነሱም በአገሬው አጠራር ሙሪድ ይባላሉ፡፡

ሙሪድ ባለበት ወይም የሚገኝበት አዋችም ሆኑ ኢናያች ኃላፊነት የሚሰማው ጎብኚዎችን ማስተማር /ማስረዳት/ የሚችል ቦታውን ከጉዳት የሚጠብቅ ሆኖ ባብዛኛው ከቅድመ አያቶች ሲወርድ የተያያዘ የሥጋ ዝምድና ያላቸው ናቸው፡፡

የዚያራ ትግበራ ለጉብኘት ወደ አዋች የሚሄዱ ግለሰብ እንደአቅሙ /ችሎታው/ ስጦታ ያበረክታሉ፡፡ ይህም ገቢ ለአስተዳዳሪዎች እንዲሁም ለምስኪኖች በሙሪዱ አማካይነት ይከፈላል፡፡ ስጦታን የማበርከት ግዴታ በማንም ጎብኚ የለበትም፡፡ መጠኑም በሰጪው ፍላጎት መሠረት ነው፡፡

ሐረሪዎች ንፁህ ናቸው፡፡ ቤታቸውንና አካባቢያቸውን በየዕለቱ የማፅዳት ባሕል አላቸው፡፡ ንፁህ አካባቢ ማራኪ መአዛ ማጠን ልምዳቸው፤ በአዋችም ሆነ በኢናያች ይስተዋላል፡፡ በንፁህና ማራኪ መአዛ በታወደው ቦታ መንፈሳዊ ጥንካሬን በማበረታታት ወደ ፈጣሪያቸው አቤት ይላሉ፡፡ ለዚህም ነው እጣን ከቤታቸው የማያጡት፡፡ በየአዋቹም በዚሁ የሚታወደው ለሙስሊሙ ዱአ ማድረግ ከሃይማኖታዊ ተግባራት መካከል አንዱ ነው፡፡ ዱአ ማለት ከፈጣሪ በጎን ለማግኘት የሚደረግ ፀሎት ማለት ነው፡፡ ዱአ ለማድረግ ደግሞ መልካም ጠረንና ደስታን የሚያውድ፣ መንፈስን ወደ ፈጣሪ ልብን የሚያረጋጋ ሽታ አስፈላጊ በመሆኑ ዕጣን /ሊባነት/ ዑድ ለዚህ ያገለግላሉ፡፡
(መፍቱህ ዘከሪያ እብዱላሂ ኑር፤ የከተማ ባሕል መፍለቂያ፣ 2000

Comments (0)
Write comment
Your Contact Details:
Comment:
[b] [i] [u] [url] [quote] [code] [img]   
:D:angry::angry-red::evil::idea::love::x:no-comments::ooo::pirate::?::(
:sleep::););)):0
Security
Please input the anti-spam code that you can read in the image.
Powered by !Harar Network
 

Your are currently browsing this site with Internet Explorer 6 (IE6).

Your current web browser must be updated to version 7 of Internet Explorer (IE7) to take advantage of all of template's capabilities.

Why should I upgrade to Internet Explorer 7? Microsoft has redesigned Internet Explorer from the ground up, with better security, new capabilities, and a whole new interface. Many changes resulted from the feedback of millions of users who tested prerelease versions of the new browser. The most compelling reason to upgrade is the improved security. The Internet of today is not the Internet of five years ago. There are dangers that simply didn't exist back in 2001, when Internet Explorer 6 was released to the world. Internet Explorer 7 makes surfing the web fundamentally safer by offering greater protection against viruses, spyware, and other online risks.

Get free downloads for Internet Explorer 7, including recommended updates as they become available. To download Internet Explorer 7 in the language of your choice, please visit the Internet Explorer 7 worldwide page.