No account yet?
Written by Administrator    Wednesday, 07 October 2009 17:00    PDF Print E-mail
በዋሽንግተን በርካታ ኢትዮጵያውያንና...
Hear this article

በዋሽንግተን በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በታክሲ ሥራ ፈቃድ ሙስና ተከሰሱ
(በጋዜጣው ሪፖርተር)

አላግባብ በሆነ መንገድ የታክሲ ሥራ ፈቃድ ለማግኘት ሲሉ የዋሽንግተን ከተማ የታክሲ ኮሚሽን ሊቀመንበርን ጉቦ በመስጠት አሲረዋል ያላቸውን 39 ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያንና ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ትውልድ ባላቸው ላይ አቃቤ ሕግ አርብ ዕለት ክስ መሰረተ፡፡

ወደ 330ዢ000 የአሜሪካ ዶላር ይጠጋል በተባለው በዚህ የጉቦ ቅሌት ዋነኛ አቀነባባሪዎችና መሪዎች ተብለው የተከሰሱት ግለሰቦች የ51 ዓመት ዕድሜ ያለው ይትባረክ ስዩሜ፣ የ47 ዓመት ዕድሜ ያለው ብርሃነ ለገሠና የ53 ዓመቱ አማኑኤል ግርማጽዮን እንደሆኑ በአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር የዋሽንግተን አቃቤ ሕግ ያወጣው መግለጫ ያሳያል፡፡

የተቀሩት 36 ግለሰቦች በከተማዋ የታክሲ አሽከርካሪዎች ሲሆን እነዚህኞቹ የተከሰሱት ደግሞ በነፍስ ወከፍ የታክሲ ባለቤትነት ፈቃድ በጉቦ ለማግኘት በመሞከር ተጠርጥረው ነው፡፡

ከጠቅላላው 330ዢ000 ዶላር ውስጥ 220ዢ000ውን ሶስቱ ግለሰቦች የሰጡ እንደሆነና የተቀረውን 110ዢ000 ዶላር ደግሞ 36 የታክሲ አሽከርካሪዎች እንደሰጡ ሪፖርተር ያገኘው የክስ ቻርጅ ያሳያል፡፡

ግለሰቦቹ ክሱ ሊመሰረትባቸው የቻለው የዋሽንግተን ከተማ የታክሲ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሊዮን ስዌይን ጉዳዩን ከሦስት ዓመት በፊት ለመንግሥት አሳውቀው ከፌዴራሉ የምርምር ቢሮ (FBI) ኤፍ.ቢ.አይ ጋር በስውር በተደረገ ክትትል መሆኑንም የዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡
    
በማቀነባበሩ ሂደት የተከሰሰቱትን ሶስቱን ግለሰቦች ጨምሮ 25ቱ ተከሳሾች ሰኞ ዕለት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ አይደለንም ብለው የዕምነት ክህደት ቃል ሰጥተዋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ፣ ባለፈው ሳምንት የዋሽንግተን ምክር ቤት አባል የጂም ግራሃም፣ ጽህፈት ቤት ሹም ቴዲ ሎዛ ታስረዋል፡፡

ቴዲ ሎዛ ከተከሳሾቹ የ1ዢ500 ዶላር ጉቦ በመቀበል የታክሲ ፈቃድ አሰጣጥ ሕግን በማስቀየር ሙከራ ወንጀል ተጠርጥረው እንዲታሰሩ ተወስኗል፡፡

"ይህ ክስ በጣም ብርቱና አሳሳቢ ነው፡፡ የታክሲ ኢንዱስትሪያችን መሠረት እያናጋ ያለውን የሙስና ችግር የሚያሳይ ነው፡፡ ሙስናን ከስር መሠረቱ ለመንቀል በአስተዳደራችን ያለውን ቁርጥ አቋቋምም የሚያሳይ ነው" ሲሉ የዋሽንግተን ተጠባባቂ አቃቤ ሕግ ተናግረዋል፡፡

የዋሽንግተን የኤፍ ቢ አይ ቢሮ ኃላፊ በበኩላቸው "የታክሲ ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት የብርና የጉቦ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የተሣፋሪዎች ደህንነትም ጉዳይ ነው" በማለት የጉዳዩን አሣሣቢነት ገልፀዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የዋሽንግተን ከተማ ምክር ቤት ተመራጭ የቴዲ ሎዛ አለቃ ጂም ግራሀም በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2004 ለአንድ ወር በኢትዮጵያ ቆይታ አድርገው ነበር፡፡

እንደ ዋሽንግተን ፖስት ዘገባ የጂም ግራሀም ጉብኝት አብዱ ጫሙ በተባሉ ኢትዮጵያዊ የተመቻቸ እንደነበርና የጂም ግራሀም የአውሮፕላን ወጪ በኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ቆይታቸው ደግሞ በሸራተን አዲስ እንደተሸፈነ አቶ አብዱ በጊዜው ለጋዜጠኞች ተናግረው እንደነበር ዋሽንግተን ፖስት ይገልፃል፡፡

አብዱ ጫሙ ከጂም ግራሀም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው የተለያዩ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡

ሐሙስ እለት የኤፍ ቢ አይ ሰዎች የግራሀምን ቤት በርብረው ብዛት ያላቸው ሳጥኖችን ይዘው መውጣታቸውንም የዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡

ግራሃም ከቴዲ ሎዛ ጋርም ይሁን ከተከሳሾቹ ጋር በወንጀል ሥራ ላይ እንዳለተሳተፉ ተናግረዋል፡፡

"ሚስተር ሎዛ ስለዚህ ጉዳይ አንድም ጊዜ አናግሮኝ አያውቅም፡፡ ጉዳዩ በተነሳበት ስብሰባ ተሳትፎ ሊሆን ይችላል፡፡ ለእኔ ግን የታክሲ ፈቃድ አሰጣጥን ሕግ በሚመለከት አንድም ጊዜ አማክሮኝ አያውቅም" ብለዋል ግራሃም፡፡

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ስለ ጂም ግራሃም ጉብኝት ተጠይቆ "ስለ ጉዳዩ ምንም መረጃ የለኝም" ብለዋል፡፡

"አልመጡም ነው ወይንስ ስለመምጣታቸው መረጃ የለንም ነው የምትሉት?" ለሚለው ጥያቄ የኤምባሲው ምላሽ "ግለሰቦች፣ ተመራጮች እንኳን ቢሆኑ፣ በግላቸው የሚያደርጉት ጉብኝትን በሙሉ አንከታተልም" ነበር፡፡  

ሙስናዉን በማቀነባበር የተከሰሱት ሶስት ግለሰቦች የክስ ቻርጅ ለማየት እዚህ ይጫኑ

የ36ቱን ሌሎች ተከሳሾች የክስ ቻርጅ ከዚህ ያንብቡ

Comments (0)
Write comment
Your Contact Details:
Comment:
[b] [i] [u] [url] [quote] [code] [img]   
:D:angry::angry-red::evil::idea::love::x:no-comments::ooo::pirate::?::(
:sleep::););)):0
Security
Please input the anti-spam code that you can read in the image.
Powered by !Harar Network
Last Updated ( Friday, 13 November 2009 16:22 )
 
Your are currently browsing this site with Internet Explorer 6 (IE6).

Your current web browser must be updated to version 7 of Internet Explorer (IE7) to take advantage of all of template's capabilities.

Why should I upgrade to Internet Explorer 7? Microsoft has redesigned Internet Explorer from the ground up, with better security, new capabilities, and a whole new interface. Many changes resulted from the feedback of millions of users who tested prerelease versions of the new browser. The most compelling reason to upgrade is the improved security. The Internet of today is not the Internet of five years ago. There are dangers that simply didn't exist back in 2001, when Internet Explorer 6 was released to the world. Internet Explorer 7 makes surfing the web fundamentally safer by offering greater protection against viruses, spyware, and other online risks.

Get free downloads for Internet Explorer 7, including recommended updates as they become available. To download Internet Explorer 7 in the language of your choice, please visit the Internet Explorer 7 worldwide page.